Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ለቀድሞ አመራሮቹ የዕውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ባሉት ዓመታት አየር መንገዱን በሥራ አስኪያጅነት እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመሩ አመራሮች የዕውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ፣ ካፒቴን ዘለቀ ደምሴ ፣አህመድ ኬሎ (ዶ/ር) ፣ አቶ ብስራት ንጋቱ ፣ አቶ ግርማ ዋቄ እና አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

እውቅና እና ሽልማቱ የተሰጠው አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስኪያጅነትና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በመሩባቸው አመታት ላበረከቱት የማይተካ የመሪነት ሚና እና አየር መንገዱ ላገኘው ስኬት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.