ሊቨርፑል ተጋጣሚውን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በርካታ ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከሦስቱ ጨዋታዎች ቀደም ብሎ በተደረገው መርሐ-ግብር በሜዳው በርንማውዝን ያስተናገደው ኒውካስል ዩናይትድ 4 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
እንዲሁም በተመሳሳይ ሠዓት በተደረጉት ጨዋታዎች ÷ ዌስትሃም ዩናይትድ በክሪስታል ፓላስ እና ሌስተር ሲቲ በፉልሃም በተመሳሳይ ውጤት 2 ለ 0 ተረትተዋል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሠንጠረዥ መሪ ሊቨርፑልን ያስተናገደው ብሬንትፎርድም 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 2 ሠዓት ከ30 ላይ አርሰናል ከአስቶንቪላ ጋር በኤሚሬትስ ስታዲየም የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡