ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አርባ ምንጭ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ÷ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች ኢስማኤል አብዱል ጋንዩ (በራስ ላይ) እና ፍፁም ጥላሁን (በፍፁም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል፡፡
ሁለቱም ግቦች የተቆጠሩት በሁለተኛው አጋማሽ ነው፡፡
በሌላ ጨዋታ ስሑል ሽረ በአርባ ምንጭ ከተማ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ከእረፍት መልስ የተቆጠረችውን የአርባምንጭ ከተማን ግብ ቡታቃ ሸመና ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡