አርሰናል እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤምሬትስ ስታዲየም የተደረገው የአርሰናል እና አስቶንቪላ ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
ይህን ጨዋታ አርሰናል ማርቲኔሊ በ35ኛው እና ሀቨርትዝ በ55ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሲመራ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ቴሌማንስ በ60ኛው እንዲሁም ዋትኪንስ በ68ኛው ግብ ማስቆጠራቸው ተከትሎ የመድፈኞቹ መሪነት ከ13 ደቂቃ በላይ ሳይዘልቅ ቀርቶ፤ አቻ ለመለያየት ተገድዷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ50 ነጥብ ሊጉን ከሚመራው ሊቨርፑል በሥድስት ነጥብ ዝቅ ብሎ አርሰናል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ አስቶንቪላ ደግሞ በ36 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡