Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በጎንደር ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጭ ሀገር እንግዶችን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በአፄ ፋሲለደስ ባህረ ጥምቀት በተከናወነው የጥምቀት ስነ ስርዓት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬና ሌሎች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በባህረ ጥምቀቱ ዙሪያ ደምቀው በሚታዩ ካህናትና ሊቃውንት የፀሎት፣ የወረብና ዝማሬ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በሙሉጌታ ደሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.