Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የቲክቶክ አገልገሎት ተቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክቶክ የብሔራዊ ጸጥታ አደጋ በመደቀኑ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ መስጠቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የቲክቶክ አገልገሎት ተቋርጧል።

በመሆኑም መተግበሪያው ከሰዓታት በፊት አገልግሎት በማቋረጡ ተጠቃሚዎቹ መተግበሪያውን መጠቀም እንደማይችሉ መልዕክት ተላልፎላቸዋል፡፡

የቲክቶክ ተጠቃሚዎች እንደገለፁትም ክልከላውን ተከትሎ መተግበሪያው ከጉግል ስቶር እና ከአፕል ስቶር ወጥቷል፡፡

የጆ ባይደን አስተዳደር ያስተላለፈውን የእገዳ ውሳኔ በቀጣይ ሰኞ ወደ ኋይትሀውስ የሚገቡት የአሜሪካ 47ኛው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክን ወደ ነበረበት ለመመለስ እንደሚሰሩ መግለፃቸው ተመላክቷል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ የቲክቶክን ጠቀሜታ መገንዘባቸውና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን እንዲያዘገይ ጠይቀው የነበረ ሲሆን ጉዳዩን በድርድር እፈታዋለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.