Fana: At a Speed of Life!

ጥምቀት የሰላም ነጋሪት የተጎሰመበት በዓል በመሆኑ ሰላምን በተግባር መኖር ይገባል- አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥምቀት የሰላም ነጋሪት የተጎሰመበት በዓል በመሆኑ እርስ በርስ በመከባበር ሰላምን በተግባር መኖር እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።

ጥምቀት በጎንደር ፋሲለደስ ባህረ ጥምቀት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

አቶ አረጋ ከበደ በክብረ በዓሉ ላይ እንደገለጹት÷ከለውጡ መንግሥት ወዲህ የጎንደር ከተማን የሚመጥኑ በርካታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው።

በመንገድና በውሃ ፕሮጀክት መሰረተ ልማት እንዲሁም በፋሲል ግንብ እድሳት የታየው ለውጥ የዚህ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።

ጥምቀት የሰላም የፍቅር የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን በመረዳት ሁሉም አካላት ለሰላም ዘብ መቆም እንዳላባቸው መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ቻላቸው ዳኜው በበኩላቸው ጎንደር የጥር ሙሽራ መሆኗን አውስተው÷ደምቃና አብባ ጥምቀት መገለጫዋ መሆኑን እያሳየች ነው ብለዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.