Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡

አርቲስቱ የእግር እሳት፣ ሥርየት፣ ሰው ለሰው፣ መንጠቆ ቴአትር እና ሌሎች የቴሌቪዥን ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ በትወና መሳተፉን የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

በአዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ የተወለደው አርቲስት እንቁስላሴ ÷በኢትዮጵያ የሲኒማ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጧል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ የሶስት ወንድ እና ሶስት ሴት ልጆች አባት የነበረ ሲሆን÷አስራ ሁለት የልጅ ልጆችንም አይቷል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለአርቲስት እንቁስላሴ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.