ወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቡድኖቹ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል መቐለ 70 እንደርታ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ምሽት12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡