Fana: At a Speed of Life!

እስራኤልና ሃማስ እስረኞችን ተለዋወጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤልና ሃማስ ባደረጉት የእስረኞች ልውውጥ 90 ፍልስጤማውያን እና ሦስት እስራኤላውያን እስረኞች ቤተሰቦቻቸውን መቀላቀላቸው ተሰምቷል፡፡

እስራኤል እና ሃማስ ሣምንታትን ከፈጀ ድርድር በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

በሁለቱ ወገኖች መካከል ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ በነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያው ምዕራፍ 90 የፍልስጤም እስረኞች መፈታታቸውን የእስራኤል ማረሚያ ቤት አስታውቋል።

ከተፈቱት እስረኞች መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ ሦስት እስራኤላውያን እስረኞች የተኩስ አቁም ስምምነት ከተጀመረ ከሰዓታት በኋላ መፈታታቸውንም ነው ቢቢሲ የዘገበው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.