Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በ900 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ይሰራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በ900 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደሚከናወን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ኡመር ገልጸዋል።

የዘንድሮውን የተፋሰስ ልማት ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት በክልሉ ከሚገኙ የገጠር ወረዳ አመራሮች፣ ከግብርና ባለሙያዎችና ሌሎች አካላት ጋር ተካሂዷል።

በዚህም ወቅት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ እንዳሉት÷ በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የደረቁ ምንጮች እንዲመለሱና የአፈር መሸርሸር እንዲቀንስ በማድረግ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብት አድርጓል።

ዘንድሮም በሶስት የገጠር ወረዳዎች በ16 ተፋሰሶች ላይ 900 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደሚከናወን አስረድተዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.