Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሕመድ ሽዴ ከተለያዩ የቻይና ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ የቻይና ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ልዑኩ ከቻይና ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪና ንግድ ባንክ፣ ከቻይና ልማት ባንክ፣ ከቻይና ኮሙኒኬሽንና ኮንስትራክሽን ኩባንያ እንዲሁም ኤግዚም ባንክ ሃላፊዎች ጋር ነው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረው፡፡

በዚህም የኢትዮጵያና ቻይናን የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክሩ የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፎች ላይ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቻይና የሥራ ጉብኝት እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.