Fana: At a Speed of Life!

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓል ሲመት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ካፒቶል ሂል አደራሽ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በበዓለ ሲመቱ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ደብሊው ጆርጅ ቡሽ፣ ባራክ ኦባማ እንዲሁም የቀድሞ ዴሞክራት እጩ ሄላሪ ክሊንተን ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ ተሰናበቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ፊት ለፊት የተገኙ ሲሆን÷በነጩ ቤተ መንግስት የመጨረሻ ቡናቸውን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ጠጥተዋል፡፡

የቀድሞ አሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ እና ሚሸል ኦባማ በፕሬዚዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ያልተገኙ እንስት ባለስልጣናት ናቸው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ከበዓለ ሲመታቸው ማግስት በሜክሲኮ ድንበር የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚያውጁ አስታውቀዋል፡፡

አስተዳደራቸው ለአንድነትና ለነፃነት እንደሚሰራ ገልጸው÷አፍሪካ አሜሪካውያንና እስያ አሜሪካውያን ከሌሎች አሜሪካውያን ባልተለየ መልኩ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ገልፀዋል፡፡

የአሜሪካን ገቢ አቅም ለማሳደግ ከሀገር ውስጥ ታሪፍና ግብር ይልቅ ከውጪ ሀገር ወደ አሜሪካ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ እንደሚጥሉ ጠቁመዋል፡፡

አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ዲፕሎማሲ በሰላም ላይ ተመሰረተ መሆኑን ጠቅሰው÷ቢሮ ከመግባታቸው አስቀድመው በእስራኤልና ሃማስ መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ ግፊት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በምርጫ ሒደት ከሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራ የተረፉት ዶናልድ ትራምፕ÷ አሜሪካን ሃያል ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የካቢኔ አባሎቻቸው የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ በትኩረት እንዲሰሩ ያዘዙ ሲሆን÷ አሜሪካ የፓናማ ቦይን መልሳ እንድትወስድ እንደሚሰሩም አስገንዝዋል፡፡

እንዲሁም ከአሜሪካ ጦር አላግባብ የተባረሩ ወታደሮች ከካሳ ክፍያ ጋር ወደ ሥራቸው እንደሚመልሱና ሃያል የሆነ  ወታደራዊ ተቋም እንደሚገነቡ ነው የተናገሩት፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ወርቃማው ዘመን አሁን ጀምሯል ሲሉ መናገራቸውንም የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.