Fana: At a Speed of Life!

በዳርፉር 20 አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18 2012 (ኤፍ..ሲ) ታጣቂዎች በሱዳን ዳርፉር በከፈቱት ጥቃት 20 አርሶ አደሮች መግደላቸውን የጎሳው መሪ አስታወቁ።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አርሶ አደሮች ከዓመታት በኋላ በዳርፍር የሚገኘውን የእርሻ ማሳቸውን እየጎበኙ በነበረበት ወቅት ነው።

በጦር ቀጠናነቱ በሚታወቀው በዚህ ስፍራ የነበሩ አርሶ አደሮች የእርሻ ማሳዎችን ለዓመታት በነበረው ጦርነት ምክንያት ተነጥቀው ቆይተዋል።

ለሁለት ወራት በፊትም የሀገሪቱ መንግስት የመሬቱ ባለቤቶችን እና የአርሶ አደሮቹን መሬቶች የቀሙ ሰዎችን በማወያየት ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

በስምምነቱ መሰረተም አርሶ አደሮቹ  መሬቶቻቸውን  በሚጎበኙበት ወቅት ታጣቂዎች ጥቃት ከፍተው 20 ሰዎች መግደላቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ከሟቾቹ መካከል ሰቶች እና ህፃናት እንደሚገኙበት ተዘግቧል።

ከ20 በላይ ሰዎች ደግሞ በጥቃቱ የቆሰሉ ሲሆን ክእነዚህም መካከል የተወሰኑት ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.