ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ቀን 9:00 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለሐዋሳ ከተማ ናትናኤል ዘለቀ እንዲሁም ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እስራኤል እሸቱ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
የሊጉ መርሐ-ግብር ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ፋሲል ከነማ እና መቻል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡