Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡

 

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6ወራት የገቢ አሰባሰብ በእቅዱ መሰረት በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን እና በቀሪ ስድስት ወራት በእቅድ የተያዘውን የገቢ እቅድ ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ግብረሀይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

 

በተጨማሪም ለገቢ አሰባሰቡ አጋዥ የሆኑ የስጋት ስራ አመራር ስርዓትን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የውዝፍ እዳ ክትትል ማጠናከር፣የጉምሩክ ዋጋን ወቅታዊ ማድረግ፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎችን ማጠናከር፣ አዳዲስ ታክስ ከፋዮች ወደ ታክስ ስርዓቱ እንዲገቡ ክትትል ማድረግ፣ የደረሰኝና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር ግብረሀይሉ የቀጣይ ወራት አቅጣጫዎች ናቸው ተብሏል፡፡

 

የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ከፕላን እና ልማት፣ ከገንዘብ፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና  ከጉምሩክ ኮሚሽን በተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ግብረ ሀይል ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.