Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በ783 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ሎጊያና ሚሌ ከተሞች በ783 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡና ከ160 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሁለት የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።

 

ፕሮጀክቶቹ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ርኢ/ር) እና የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ ኤልያስ(ፕ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቀዋል።

 

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የክልሉ ህዝብ ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል።

 

እንደ አፋር ላለ ሞቃታማ ክልል ውሃ ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ ፕሮጀክቱን በአግባቡ መጠቀምና በፍትሃዊነት ማዳረስ እንደሚገባ ገልጸዋል።

 

የውሃና አነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በበኩላቸው÷ ፕሮጀክቶቹ ከንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ባሻገር ለከተሞቹ የተለያዩ አገልግሎቶችን በማሳለጥ የህዝብ ተጠቃሚነትን ያጎለብታሉ ብለዋል።

 

የክልሉ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሻሚ በበኩላቸው÷ፕሮጀክቶቹ በሁለቱ ከተሞች ለበርካታ ዓመታት ሲያጋጥም የቆየውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር እንደሚያቃልል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.