Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ከ12 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር ኢ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት ÷በክልሉ 12 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግባቸው 158 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው።

በዚህ አመት 95 ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ታስቦ እየተሰራ መሆኑንና 22ቱ ወደ ስራ መግባታቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።

በዚህም በጥቅሉ 26 ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማ መሆኑን የገለጹ ሲሆን÷ ክልሉ አሁን ላይ 85 ሺህ ሄክታር መሬት የሚያለሙ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እያስጠና መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በክልሉ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት የሚቻል ቢሆንም እስከ አሁን ማልማት የተቻለው ግን እስከ 250 ሺህ ሄክታር መሬት ብቻ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.