Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይሉን ከአፍሪካ ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አየር ኃይሉን ከአፍሪካ አየር ኃይሎች ቀዳሚ ለማድረግ በከፍተኛ ንቅናቄ እየተሰራ መሆኑን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡

ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ከ15ኛ ዙር መደበኛ ተማሪ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዋና አዛዡ በዚህ ወቅት÷ አየር ኃይል የሀገር ኩራት የህዝብ አለኝታ መሆን እንዲችል ተደርጎ ተገንብቷል ብለዋል፡፡

ተቋሙ የአመራሮችን አቅም የሚያጎለብቱ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው በዚህም ብቃትና ጥራት ያላቸውን ተተኪ ወታደራዊ አመራሮች እያፈራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ከፍተኛ መኮንኖቹ የአየር ኃይሉን የለውጥ ጉዞና አሁናዊ ወታደራዊ ቁመናውን እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅሙን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.