የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ቦሉ ግዛት በእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ቦሉ ግዛት በተከሰተ የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡት ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግሥት እና ህዝብ ጎን እንደምትቆም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
ዛሬ ማለዳ በሰሜናዊ ቱርክ ቦሉ ግዛት ካርታልካያ ሪዞርት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 66 ሰዎች ሲሞቱ 51 ሰዎች ቆስለዋል።
እሳቱ በአሁኑ ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋሉንም ቲአርቲ በዘገባው አስታውሷል፡፡