Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በአወሊያ የልማትና እርዳታ ማዕከል የችግኝ ተከላ አከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋር በመተባበር በአወሊያ የልማትና እርዳታ ማዕከል የችግኝ ተከላ አከናወነ።

በዕለቱ 1000 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 60 በመቶዎቹ ለምግብነት የሚውሉ ናቸው።

በችግኝ ተከላው ላይም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሃላፊዎች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሃጂ ኡመር እድሪስ ለዚህ በጎ አላማ ላይ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።

ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሃጂ ዑመር እድሪስ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት በስኬት በማጠናቀቋ ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በተጨማሪም ወቅቱ ፈታኝ በመሆኑ ሁሉም ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቅ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት የችግኝ ተካላ የተከናወነበት የአወሊያ የልማትና እርዳታ ማዕከል 68 አመታትን ያስቆጠረና በትምህርት፣ በጤና፣ ወላጅ አልባ ህጻናትን በማሳደግ እንዲሁም በሌሎችም መስኮች ላይ የተሰማራ ተቋም ነው።

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.