Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነሱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነሱን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ  ገለጹ።

አዲስ አበባ- አዳማ የፍጥነት መንገድ መግቢያ ላይ “የትራፊክ አደጋ ሰለባዎችን እያሰብን አረንጓዴ አሻራችንን እናኑር!” በሚል መሪ ቃል ደም የመለገስ የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ የትራፊክ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት በ2011 በጀት ዓመት የተመዘገበው 4ሺህ 597 ሞት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ 3ሺህ 400 ቀንሷል ብለዋል።

የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎችን እያሰብን አረንጓዴ አሻራ የምናሳርፍበትና በዚህም የነገ ተስፋን እናመላክታለን ብለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አደጋን መቀነስ የተቻለው በአገር አቀፍ ደረጃ “#እንደርሳለን በሚል መሪ ሐሳብ በሚዲያ ንቅናቄ መድረኮች፣በሕግ ማስከበርና በመንገድ ደህንነት ዘርፍ በተሰሩ ሥራዎች ነው” ብለዋል።

አደጋውን  ሙሉበሙሉ ለማስቀረት በ”ይቻላል”መንፈስ እየተከናወኑሥራዎችን በተለይም ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ ያጎናፀፈውን መነቃቃት ትምህርት ሊወሰድበት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በአንድ ጀምበር የሚመጣ ለውጥ ባለመኖሩ በፅናትና ቀጣይነት ባለው መልኩ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ ሲሉም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡም እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የስድስት  ዓመት ልጃቸውን በትራፊክ አደጋ ያጡት አቶ ደረጀ ግርማ ኅብረተሰቡና አሽከርካሪዎች የትራፍክ አደጋ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ችግር በመረዳት የትራፊክ ደህንነት ሕጎችን ማክበር ይገባዋል ብለዋል።

የትራፊክ አደጋ አስከፊ በመሆኑ እያንዳንዱ ማህበረሰብ በጥንቃቄና በማስተዋል መጓዝ አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የትራፊክ አደጋ የደረሰባቸው አቶ አዲስ ዘመኔና አቶ ኃይሉ ዓለማየሁ ናቸው።

የትራፊክ አደጋ በእኛ ይብቃ ያሉት አስተያየት ሰጪዎች ችግሩን ለማቃለል በ”ይቻላል” መንፈስ መንቀሳቀስ አለበትብለዋል።

የበለፀገች ኢትዮጵያን አውን ለማድረግ ዋነኛ አቅም የሆነውን ክቡሩን የሰው ሕይወት የሚቀጥፈውን የትራፍክ አደጋ ለመከላከል ዜጎች ድርሻቸውን እንዲወጡ በመርሐ ግብሩ ላይ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.