Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያ የኮሮናቫይረሰ ተጠርጣሪ ማግኘቷን ተከትሎ በድንበር አካባቢ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሮያ በሀገሯ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠረ ሰው መገኘቱን አስታውቃለች።

የኮሮና ቫይረስ በዓለማችን ላይ በተለይም በቻይናዋ ዉሃን ከተገኘ ሰባት ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ ሰሜን ኮሪያ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በቫይረሱ የተጠረጠረ ሰው አገኘሁ እያለች ያለው።

ይህንን ተከትሎም የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በድንበር አቅራቢያ በሚገኙ ከተሞች ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም በሰሜን ኮሪያ የድንበር ከተሞች የሰዎችም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዲገደቡም ነው ኪም ጆንግ ኡን ትእዛዝ ያስተላለፉት ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈችው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተጠረጠረ ሰው በህገ ወጥ መንገድ ከደቡብ ኮሪያ ድንበር አቋርጦ መግባቱን ተከትሎ እንደሆነም ታውቋል።

ግለሰቡ ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ከተረጋገጠም በሰሜን ኮሪያ ቫይረሱ የተገኘበት የመጀመሪያው ሰው እንደሚሆንም ነው እየተነገረ ያለው።

ምንጭ፦ reuters.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.