Fana: At a Speed of Life!

የልብ ህክምናን ለማሻሻል የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኽርት አታክ ኢትዮጵያ የልብ ህክምናን ለማሻሻል እና በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው የሦስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ፈረሙ፡፡

ለሦስተኛ ዙር ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ የመጣውን የሃኪሞች ቡድን በጽህፈት ቤታቸው የተቀበሉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ÷ ቡድኑ እየሰጠ ስለሚገኘው በጎ ተግባር በተገልጋዩ ህብረተሰብ አመስግነዋል፡፡

የስምምነቱ መፈረም በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የልብ ህክምና ለማሳደግ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የኽርት አታክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኦብስኔት መርዕድ ÷ኽርት አታክ ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከአየር መንገዱ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ የሃኪሞች ቡድኑ የሚሰጣቸውን የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ለማስፋትና ኢትዮጵያውያን ሃኪሞችን ለማሰልጠን እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ለማ ናቸው፡፡

ኽርት አታክ ኢትዮጵያ ለሚሰጠው አገልግሎት አየር መንገዱ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

የስምምነቱ መፈረም በኢትዮጵያ እየተሰጠ የሚገኘውን የልብ ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚረዳ በፊርማ መርሐ-ግቡሩ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.