Fana: At a Speed of Life!

ቪፓር የተሰኘ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ መሠማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንዱ ቪፓር የተሰኘ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ መሠማራት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴዔታ ሀሰን መሀመድ ከኩባንያው ተወካዮች ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የሕንድ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ከማስፋፋት ባሻገር በሀገራቱ መካከል ከፍተኛ የኢኮኖሚና የባህል ትስስር እንደሚፈጥር ሚኒስትር ዴዔታው ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው ከ16 በላይ በሆኑ ሀገራት ተሽከርካሪ በማምረት ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያም የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለማምረትና በነዳጅ የሚሠሩትን ወደ ኤሌክትሪክ በመቀየር ሥራ ላይ እንደሚሰማራ መገለጹን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኩባንያው የወጪና ገቢ ምርትን ከመተካት አኳያ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን÷ በቀጣይ የትግበራ ሂደቶችን በተመለከተ ተጨማሪ ውይይቶች እንደሚኖሩ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.