Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ ከማዕድን ዘርፍ ከ58 ሚሊየን ብር በላይ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሥድስት ወራት ከ25 ቶን በላይ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ለገበያ በማቅረብ ከ58 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውኃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም 77 ሺህ 333 ቶን የድንጋይ ከሰልና ዶሎማይት በማምረት ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ማቅረብ መቻሉን የቢሮው ምክትል እና የማዕድን ዘርፍ ኃላፊ ሔለን ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ ያለውን ሃብት ለይቶ ለልማት ለማዋልም ከአርባምንጭ እና ከዲላ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እየሠራን ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡

በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ለ10 ሺህ 100 ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ጠቅሰዋል፡፡

ከዘርፉ የተገኘው ውጤት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ዕድገት ማሳየቱን ገልጸው÷ በቀጣይ ሃብቱን ከብክነት በመከላከል ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ርብርብ ይደረጋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.