ከኢኮኖሚ ዞኖችና ድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ውስጥ ባለፉት 6 ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ መገኘቱን ተገለጸ፡፡
የኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ከ72 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ወደ ወደ ውጭ ለመላክ አቅዶ እንደነበር ተገልጿል፡፡
የዕቅዱን 73 በመቶ መፈተም እንደተቻለ የከገለጸው ኮርፖሬሽኑ÷ ቦሌ ለሚ፣ ሐዋሳ እና አዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከፍተኛውን ደረጃ ይዘዋል ብሏል፡፡
በአተቃላይ ከተላኩት ምርቶች መካከልም አልባሳትና ጨርቃጨርቅ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከ24 ሺህ ለሚልቁ ወገኖች የሥራ ዕድል መፈጠሩም ተጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል የሀገር ውስጥ አምራቾች ከውጭ ሀገር አምራቾች ጋር በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ35 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል ተብሏል፡፡