Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ ሚ ዐቢይ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ መኪና በስጦታነት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተበረከተላቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀዩንዳይ ፕሬዚዳንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ ተጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርበን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

መኪናውን የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን መሙላት እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.