Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኋይት ሀውስ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሊመክሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቅርቡ በዓለ ሲመታቸውን ፈጽመው ወደ ሥራ የገቡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኋይት ሀውስ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታኒያሁ ጋር ሊመክሩ መሆኑ ተነገረ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ በቀረበላቸው በቀጣይ ሳምንት በኋይት ሀውስ የሚገናኙት ኔታኒያሁ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሥራ ከጀመሩ በኋላ የሚያገኟቸው የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ ይሆናሉ።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ሁለቱ መሪዎች በቀጣይ ሳምንት ተገናኝተው እንደሚመክሩ የኋይት ሀውስ ባለስልጣን አረጋግጠዋል።

መሪዎቹ እስራኤል እና ሀማስ የደረሱት የተኩስ አቁም ሥምምነትን በተመለከተ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀደም ብለው የጋዛ መሰረተ ልማት ዳግም እስኪገነባ ጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ ግብጽ እና ጆርዳን ፍልስጤማውያንን እንዲያስጠልሉ ያቀረቡት ምክረ ሃሳብ በሀማስ እና የፍልስጤም ባለስልጣናት ተቃውሞ እንደገጠመው ይታወቃል።

ግብጽ እና ጆርዳንም ሃሳቡን ውድቅ ያደረጉት ቢሆንም በኔታኒያሁ መንግስት በኩል ተፈጻሚ እንዲሆን ግፊት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.