Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ 64 ሰዎችን የጫነ አውሮፕላንና 3 ወታደሮችን የያዘ ሄሊኮፕተር አየር ላይ ተጋጩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ 64 ሰዎችን የጫነ አውሮፕላን እና ሶስት ወታደሮችን የያዘ ሄሊኮፕተር አየር ላይ መጋጨታቸው ተሰምቷል፡፡

የሀገሪቱ አቪዬሽን አስተዳደር እንዳስታወቀው÷ አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን ፥ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሦስት ወታደሮችን ጭኖ ነበር፡፡

የአውሮፕላን አደጋው የደረሰው ፖቶማክ የተባለ ወንዝ አቅራቢያ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡

አደጋውን ተከትሎ የመንገደኞች አውሮፕላን ፖቶማክ በተሰኘ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ የሕይወት አድን ጀልባዎች እና ጠላቂዎች የነፍስ አድን ሥራ እያከናወኑ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ አደጋው ለተደረገላቸው ማብራሪያ ለአደጋ ምላሽ ሰጪዎች ምስጋና አቅርበዋል ።

ይሁን እንጂ የዋሽንግተን ዲሲ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ጆን ዶንሊ እንዳሉት÷ አደጋው አሰቃቂና ምላሽ ለመስጠትም አስቸጋሪ ነው፡፡

አሁን ላይ 300 የሚሆኑ የነፍስ አድን ሰራተኞች በወንዙ ውስጥ ፍለጋ እደረጉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሬል ቦውሰር በበኩላቸው ፥ የነፍስ አድን ሰራተኞች በድቅድቅ ጨለማና ቅዝቃዜ ውስጥ ፍለጋቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡

በደረሰው አደጋ እስካሁን ለሕልፈት የተዳረጉ እና በሕይወት የተረፉ ሰዎችን አስመልክቶ በዘገባው የተባለ ነገር የለም፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.