Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር መቅደስ ከሜድ አክሽን ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በሜድ አክሽን ዋና ዳይሬክተር ሲልቪዮ ሊዮኒ የተመራ ልኡካን ቡድን ጋር በሚሰጣቸው የጤና አገልግሎቶች ዙርያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቀት ዶክተር መቅደስ ዳባ ÷ ጤና ሚኒስቴር ከሜድ አክሽን ጋር ለረጅም ጊዜ በትብብር ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በርካታ ህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና ለማግኝት እየተጠባበቁ እንደሚገኙም በመግለጽ ሜድ አክሽን በነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለሜድ አክሽን እንደሚያደርግም መገለጹን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሜድ አክሽን በዶክተሮች፣ ነርሶች እና ቴክኒሻኖች የበጎ ፈቃድ አስተዋፅዖ ላይ የተመሰረተ ማህበር ሲሆን ÷ ቡድኑ በሕክምናው መስክ ተስፋን እና ጤናን ለማምጣት በየቀኑ በትጋት የሚሰሩ ባለሙያዎችን ያቀፈ መሆኑን የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ሲልቪዮ ሊዮኒ ገልጸዋል፡፡

ቡድኑ ኢትዮጵያውያን ሃኪሞችን በማሰልጠን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ፥ በኢትዮጵያ የሚሰጠው የህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና አገልገሎት ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲሰጥ የበኩላቸውን ሚና አንደሚወጡም አመላክተዋል፡፡

ሜድ አክሽን በኢትዮጵያ በርካታ የልብ ቀዶ ህክምና የሚስፈልጋቸው ህጻናት ልየታን ያካሄደ ሲሆን ÷ ከጣሊያን ለመጀመሪያ ዙር የመጣ የልብ ቀዶ ህክምና ቡድን ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለህጻናት በመስጠት ላይ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.