Fana: At a Speed of Life!

በወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራ የልዑካን ቡድን የታጁራ ወደብን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራ የልዑካን ቡድን ትናንት በጂቡቲ ታጁራ ክልል ተገንብቶ ስራ የጀመረውን ወደብ ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ የጂቡቲ ትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የጂቡቲ ወደብና ነጻ ቀጠና ሊቀመንበር እንዲሁም የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የወደቡ ስራ መጀምር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ተከትሎ እየጨመረ የመጣውን የወጪ ገቢ ምርት ፍሰት ለማስተናገድ ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም ባሻገር የሁለቱን ሃገራት የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል ተብሏል፡፡

የታጁራ ወደብ በአንድ ጊዜ የሁለት መርከቦችን ጭነት የመቀበል አቅም ያለው ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እንደ ማዳበሪያ፣ ድንጋይ ከሰልና ስንዴ የመሳሰሉ ብትን ጭነቶችን እንዲሁም ሌሎች የወጪ ገቢ ምርቶችን እንደሚያስተናግድ ነው የተነገረው፡፡

ይህ ዓይነቱ ግዙፍ ፕሮጀክት የሁለቱ ሃገራት ጠንካራ የሆነ ሁለንተናዊ ግንኙነት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል በጂቡቲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.