ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 12 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሪክተር አቶ አማኑኤል ብሩ እንዳሉት÷በክልሉ ከ134 ሺህ ቶን በላይ እሸት ቡና ተሰብስቦ የደረቅ ቡና ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
በምርት ዘመኑ ተሰብስቦ የተከማቸ ቡናን በቀጣይ ሶስት ወራት አሟጦ ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም ሕገ-ወጥ የቡና ዝውውርን ከመቆጣጠር በተጓዳኝ አቅራቢዎች ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ እንዲያቀርቡ በየደረጃው ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በግማሽ ዓመቱ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን ጠቁመው÷ አምራቶች ከቡና ምርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡