እስራኤል 183 ፍልስጤማዊያን እስረኞችን ለቀቀች
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል 183 ፍልስጤማዊያን ዜጎችን ከእስር መፍታቷን አስታውቃለች፡፡
ሃማስ ሶስት እስራኤላዊያን ታጋቾችን መልቀቁን ተከትሎ ነው እስራኤል 183 ፍልስጤማዊያንን ከእስር የፈታቸው፡፡
እስረኞቹ ዌስት ባንክ ሲደርሱም በርካታ ፍልስጤማዊያን ዜጎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ቀደም ሲል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ እስራኤል 25 ፍልስጤማዊያን እስረኞችን መልቀቋን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡