Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 579 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7 ሺህ 9 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 579 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 14 ሺህ 547 ሰዎች የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ቫይረሱ ያለባቸው 7 ሺህ 931 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት 66 ፅኑ ታማሚዎች የሚገኙ ሲሆን 170 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 386 እንደደረሰም ነው ሚኒስትሯ በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት በ24 ሰዓታቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት 228 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በአጠቃላይ ለ389 ሺህ 348 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.