Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በዩክሬን የሃይል መሰረተ ልማት ላይ የተሳካ የአየር ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ በዩክሬን የጋዝ መሰረተ ልማቶች ላይ የተሳካ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የአየር ላይ ጥቃቱ ለዩክሬን መከላከያ ሰራዊት ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትን ዒላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በተፈጸመው ጥቃት እስካሁን 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን÷በርካቶች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ የጋዝ መሰረተ ልማቶችና መኖሪያ ቤቶች ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት መድረሱን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.