አርሰናል ማንቼስተር ሲቲን 5 ለ 1 አሸንፏል
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም ማንቼስተር ሲቲን 5 ለ 1 ረትቷል፡፡
የመድፈኞቹን ግቦች ኦዴጋርድ፣ ፓርቴ፣ ሌዊስ ስኬሊ፣ ሀቨርትዝ እና ንዋኔሪ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል፡፡
የውኃ ሰማያዊዎቹን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ደግሞ ኤርሊንግ ሃላንድ አስቆጥሯል፡፡
ቀደም ብለው በተካሄዱ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ማንቼስተር ዩናይትድ በክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ብሬንትፎርድ በቶተንሃም ሆትስፐር በተመሳሳይ ውጤት 2 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡