ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማዕድን ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በተዘጋጀው የ2025 የአፍሪካ ማዕድን ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
የጉባኤው ዓላማ አህጉራዊ የማዕድን ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንደሆነ ተገልጿል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ300 በላይ የማዕድን ባለድርሻ አካላት እና ከ1 ሺህ 200 በላይ ጎብኚዎች በጉባኤው መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡
በአፍሪካ የማዕድን ኢንዱስትሪ ውስጥ በትብብር ለመስራት እና የዘርፉን ኢንቨስትመንት ሚያሳድጉ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት በመድረኩ ይካሄዳል።
ለቀጣይ ሶስት ቀናት በሚቆየው ኮንፈረንስ የኢትዮጵያ ልዑክ እድሉን በመጠቀም የኢትዮጵያን የማዕድን ምርት ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኮንፈረንሱ ከማዕድን ሚኒስቴር በተጨማሪ በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም እየተሳተፈ እንደሚገኝ የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡