Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን አሸነፈ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተካሄደ የ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን አሸነፏል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም 9፡00 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ነው ማሸነፍ የቻለው።

ለኢትዮ ኤሌክትሪክ የማሸነፊያ ግቦቹን እዮብ ገ/ማርያም ፣ አቤል ሀብታሙ እና አሸናፊ ጥሩነህ አስቆጥረዋል።

ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከድሬደዋ ከተማ ይጫወታሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.