Fana: At a Speed of Life!

1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ዳፕና ዩሪያ የጫኑ መርከቦች ወደብ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን 1 ሚሊየን 100 ሺህ ኩንታል ዳፕ እና ዩሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

ይህንን ተከትሎም እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከውጭ የተጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ወደ 5 ሚሊየን 392 ሺህ 600 ኩንታል ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ውስጥ 3 ሚሊየን 717 ሺህ 212 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት ለአርሶ አደሮች በመከፋፈል ላይ ይገኛል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተጨማሪ 1 ሚሊየን 675 ሺህ ኩንታል ዳፕና ዩሪያ ማዳበሪያ የጫኑ ሦስት መርከቦች ከጥር 28 እስከ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደብ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.