Fana: At a Speed of Life!

ኔታኒያሁ እና ትራምፕ በእስራኤል-ጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት ዙሪያ ሊመክሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእስራኤል ፕሬዚዳንት ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነትና ኢራን ጉዳይ ላይ ሊመክሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

መሪዎቹ ዛሬ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትራምፕ ውይይቱን አስመልክተው ባነሱት ሃሳብ ከእስራኤል እና ከሌሎች ሀገራት ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ዙሪያ የሚያደርጉት ውይይቶች ለውጥ እያሳዩ መሆናቸውን ቢያነሱም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ሆኖም ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ እርግጠኛ አልሆንኩም በማለት “በሀገራቱ መካከል ሰላም እንደሚሰፍን ምንም ዓይነት ዋስትና የለኝም” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ዶናልድ ትራምፕ በይፋ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ለተፈረመው የተኩስ አቁም ስምምነት ምስጋና ማቅረባቸውን የአልጄዚራ ዘገባ አመላክቷል።

የእስራኤል ተደራዳሪ ቡድን በሁለተኛው ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመነጋገር በዚህ ሣምንት መጨረሻ ወደ ኳታር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡

ቡድኑ የስምምነቱ ቴክኒካዊ ዝርዝሮች ባላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይም በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ ስምምነት ሀማስ 18 ምርኮኞችን ሲለቅ እስራኤል የምታደርሰውን ጥቃት አቁማ በመቶ የሚቆጠሩ ምርኮኞችን መልቀቋ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.