Fana: At a Speed of Life!

ትብብርን በማጠናከር የሚገኙ እድሎችን ወደ ሀብትነት በመቀየር የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዲጂታል ዘርፉ ትብብርን በማጠናከር የሚገኙ እድሎችን ወደ ሀገር ሀብትነት በመቀየር የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስቴሩ ከህንድ ኤስ ኤ ኤ አር ሲ ማስትስ ቴክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በደመና ማስላት አገልግሎቶች፣ በሶፍትዌር ቴክኖሎጂና በፈጠራ ውስጥ የልህቀት ኢንተርፕራይዞች ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት በለጠ ሞላ (ዶ/ር)÷ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፉን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ህልውና መሰረት አድርጋ በምትሰራው ምዕራፍ ውስጥ ትብብርን በማጠናከር የሚገኙ እድሎችን ወደ ሀገር ሀብትነት በመቀየር የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂ ላይ ያለን አቅም አሟጦበመጠቀምና የትብብር ስራዎችን በማጠናከር እየረቀቀና እየተወሳሰበ የመጣውን የቴክኖሎጂ እድገት መቀላቀል ግዴታ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በህንድ ኤስ ኤ ኤ አር ሲ ማስትስ ቴክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አር ናዳጎፓን (ዶ/ር)÷ኩባንያው ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው መግለጻቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የተደረገው ስምምነት ግቡን እንዲመታ በተናበበና በጠበቀ ግንኙነት ስራዎች ተለይተው እንደሚሰሩም የጋራ ስምምነት ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.