ቼክ በመከላከያ ኢንዱስትሪ መስክ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ኢንዱስትሪ መስክ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ዳንኤል ብላዠኮቬትስ ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት በመከላከያውም ዘርፍ ሊንጸባረቅ እንደሚገባ በውይይቱ ገልጸዋል።
በዚሁ ውይይት የሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሪያማ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የቼክ ሪፐብሊክ የመከላከያ ምክትል ሚኒስትር በበኩላቸው÷ ሀገራቸው በመከላከያ ኢንደስትሪ መስክ ፣ በሥልጠናና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያላትን ሰፊ ተሞክሮ ለማጋራትና አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል ።