Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ ከፈረንሳይዋ ቪሌር ባን ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ከፈረንሳይ ቪሌር ባን ከተማ ከንቲባ ሴድሪክ ቫን ስቲቫንዴል ጋር ተወያዩ።

አቶ አደም በውይይቱ ቪሌር ባን እና ድሬዳዋ ከተማ ስምምነት ተፈራርመው በጋራ እየሰሩ ያሉ እህትማማች ከተሞች መሆናቸውን አንስተው ይህ ትብብር ለኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት መጠናከር ከፍ ያለ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ፈረንሳይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኑን ጠቀመው ለዚህም የኢትዮ ጁቡቲ ባቡር መስመርን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ ትብብሮች ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሴድሪክ ቫን ስቲቫንዴል በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በፈጣን ለውጥና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ መሆኗን መመልከት ችለናል ያሉ ሲሆን ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የለውጡ መንግሥት ስራዎች ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።

ከንቲባው በተለያዩ መስኮች ያሉየሁለቱ ሀገራት ትብብሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.