Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተገኝተዋል።

አቶ መሃመድ ኢድሪስ÷ሀገር እንዲገነባና በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ትስስር እንዲጠፈር የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

ሰላምን ማምጣት የመንግስት ሚና ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሰላም የሁሉም ድምር ውጤት በመሆኑ የንግዱ፣ የሃይማኖት አባቶችና ሁሉም የማህበረሰብ አካላት ሚናቸውን ሊውጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ለጋራ ትርክት ግንባታ እና ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮሩ መነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.