Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ወ/ሮ ዓለሚቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ከተረጂነት ለመላቀቅ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

በክልሉ የ2017 የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የክልሉ አመራሮች በተገኙበት በማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ወ/ሮ ዓለሚቱ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ድርሻ አላቸው።

በተለይም የተራቆቱና የተጎዱ አካባቢዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎችን በመጠናከር “የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ከተረጂነት ለመላቀቅ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተግተን ልንሰራ ይገባል” ብለዋል።

በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተፋሰስ ልማትና የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች የአካባቢ መራቆትንና የአየር ንብርት ለውጥን በመከላከል በግብርናው ዘርፍ ውጤት እንዲመጣ አስችሏል ብለዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ፓል ቱት በበኩላቸው÷138 ተፋሰሶች ላይ ከ145 ሺህ ሄክታር በላይ የተራቆተ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ለኢዜአ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.