Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል እንዲስተናገዱ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል እንዲስተናገዱ አሳስቧል፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ÷ ዛሬ ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ መከሰቱን አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን አመልክቷል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የሚጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራቸው እንዲሳፈሩ አሳስቧል፡፡

ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የሚቀጥል መሆኑንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው መጉላላትም መንገደኞችን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.