በዋና ዋና ከተሞች የአድራሻ ስርዓት ፕላትፎርም ስራ ተከናውኗል-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ከተሞች የአድራሻ ስርዓት ፕላትፎርም ቤዝ ማፕ የመስራት ስራ መከናወኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የ2017 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንግስትና የንግድ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በተያዘው እቅድ 861 ተቋማት ወደ ኤሌክትሮኒክ ግብይት መግባታቸው የተጠቀሰ ሲሆን ይህንን ለማሳለጥ የሚያስችሉ 68 የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማሳለጫ ፕላትፎርሞች መገንባታቸው ተጠቁሟል።
የግሉ ዘርፍ ተቋማት በአይሲቲና ዲጂታል ኢንደስትሪዎች ለመሰማራት በተያዘው እቅድ መሰረት 474 የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ከተሞች የተዘጋጁ የአድራሻ ስርዓት ፕላትፎርም ቤዝ ማፕ የመስራት ስራ መከናወኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።