በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የሰላም ድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫችን ሠላም ነው” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚገልጽ ሰልፍ ነው ያካሄዱት።
ነዋሪዎቹ ለትግራይ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት አያስፈልግም፤ በክልሉ ያለውን ሠላማዊ እንቅሥቃሴ እና መሠል ሥራዎች በማሥተጓጎል የሚገኝ ጥቅም የለም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ለትግራይ እና ነዋሪዎቿ ሠላም በምንም የማይተካ መሆኑን ሰልፈኞቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ እና ለሠላም ጠንቅ ከመሆን እንዲታቀቡም አስገንዝበዋል።
በሰለሞን ይታየው፣ነፃነት ፀጋዬ ና እፀገነት አምኃ