የኃይል ስርቆት በፈፀሙ የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት የኃይል ስርቆት በፈፀሙ 157 የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡
ርምጃ የተወሰደባቸው ተቋማት በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን 120፣ በደቡብ አዲስ አበባ 15፣ በሸገር ከተማ 13፣ በምዕራብ አዲስ አበባ 9 እንዲሁም በጭሮ ሪጅን አንድ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የሰሜን አዲስ አበባ 10 ሚሊየን ብር፣ ደቡብ አዲስ አበባ 4 ሚሊየን ብር፣ ሸገር 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር እንዲሁም ምዕራብ አዲስ አበባ 2 ነጥብ 4 ብር የፍጆታ ሂሳብ ማስከፈላቸው ተገልጿል፡፡
የኃይል ስርቆቱ መፈፀሙ የተረጋገጠው በተቋሙ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ መመርመሪያ ቤተ-ሙከራ ሲሆን ፥ ስርቆት የፈፀሙት ግለሰቦች ላይ የወንጀል ክስ ተመስርቶ ክትትል እየተደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡
የሃይል ስርቆት ተግባር ሲፈፅም የተገኘ አካል በሕግ ከመጠየቁም ባለፈ ይጠቀምበት የነበረው አገልግሎት እንደሚቋረጥና ያለአግባብ ለተጠቀመው የፍጆታ ሂሳብ በታሪፉ መሰረት ተሰልቶ ከዳግም ማስቀጠያ ክፍያና ከተጨማሪ ቅጣት ጋር እንዲከፈል እንደሚደረግ የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡